1 Chronicles 9

1እስራኤል ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተቈጥረው ስማቸው በእስራኤል ነገሥታት መዝገብ ላይ ሰፈረ።

የኢየሩሳሌም ከተማ ሕዝብ

9፥1-17 ተጓ ምብ – ነህ 11፥3-19 የይሁዳ ሕዝብ ከፈጸሙት በደል የተነሣ ተማርከው ወደ ባቢሎን ተወሰዱ።
2በመጀመሪያ በየርስታቸውና በየከተሞቻቸው ተመልሰው የሰፈሩት ጥቂት እስራኤላውያን፣ ካህናት፣ ሌዋውያንና በቤተ መቅደሱ ውስጥ የጕልበት ሥራ የሚሠሩ አገልጋዮች ነበሩ።

3በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ የይሁዳ፣ የብንያም፣ የኤፍሬምና የምናሴ ነገዶች የሚከተሉት ናቸው፤
4ከይሁዳ ልጅ፣ ከፋሬስ ዘሮች፣ የባኒ ልጅ፣ የአምሪ ልጅ፣ የዖምሪ ልጅ፣ የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ።
5ከሴሎናውያን፦
የበኵር ልጁ ዓሣያና ወንዶች ልጆቹ።
6ከዛራውያን፦
ይዑኤል፤
የሕዝቡ ቍጥር ስድስት መቶ ዘጠና ነበረ።
ከይሁዳ ነገድ የሰው ቍጥር ስድስት መቶ ዘጠና ነበር።

7ከብንያማውያን፦
የሐስኑአ ልጅ፣ የሆዳይዋ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ።
8የይሮሐም ልጅ ብኔያ፤ የሚክሪ ልጅ፣ የኦዚ ልጅ ኤላ፤ የይብንያ ልጅ፣ የራጉኤል ልጅ፣ የሰፋጥያ ልጅ ሜሱላም።
9በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ በተጻፈው መሠረት ከብንያም ነገድ የሕዝቡ ቍጥር ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ ወንዶች የቤተ ሰብ አለቆች ነበሩ።

10ከካህናቱ፦
ዮዳኤ፣ ዮአሪብ፣ ያኪን፤
11የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የሆነው የአኪጦብ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ።
12የመልክያ ልጅ፣ የጳስኮር ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤ የኢሜር ልጅ፣ የምሺላሚት ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የየሕዜራ ልጅ፣ የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ።
13የቤተ ሰብ አለቃ የነበሩት ካህናት ቍጥር አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ስድሳ ነበረ፤ እነዚህም በእግዚአብሔር ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት ብቁ ሰዎች ነበሩ።

14ከሌዋውያን ወገን፦
ከሜራሪ ዘሮች የአሳብያ ልጅ፣ የዓዝሪቃም ልጅ፣ የአሱብ ልጅ ሸማያ፣
15በቅበቃር፣ ኤሬስ፣ ጋላልና የአሳፍ ልጅ፣ የዝክሪ ልጅ፣ የሚካ ልጅ መታንያ።
16የኤዶታም ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሰሙስ ልጅ አብድያ። እንዲሁም በነጦፋውያን ከተሞች የኖረው የሕልቃና ልጅ፣ የአሳ ልጅ በራክያ።

17የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች፦
ሰሎም፣ ዓቁብ፣ ጤልሞን፣ አሒማንና ወንድሞቻቸው፤ አለቃቸውም ሰሎም ነበረ፤
18እርሱም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በንጉሡ በር እስካሁን ድረስ ተመድቧል። እነዚህም የሌዋውያኑ ሰፈር በር ጠባቂዎች ነበሩ።
19የቆሬ ልጅ የአብያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ ሰሎምና ከእርሱም ቤተ ሰብ የሆኑት ቆሬያውያን ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ
በዚህ በቍጥር 21 እና 23 ላይ ቤተ መቅደሱን ያመለክታል።
የሚያስገባውን በር ይጠብቁ እንደ ነበር ሁሉ፣ እነዚህም ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር።
20በቀድሞ ጊዜ የበር ጠባቂዎቹ አለቃ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ነበረ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።
21ወደ መገናኛው ድንኳን የሚያስገባውን በር የሚጠብቀው ደግሞ የሜሱላም ልጅ ዘካርያስ ነበረ።

22መግቢያ በሮቹን እንዲጠብቁ የተመረጡት በአጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

እነርሱም በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት በሚኖሩባቸው መንደሮች ተቈጥረው ተመዘገቡ፤ በር ጠባቂዎቹን በዚያ ቦታ ላይ የመደቧቸው ዳዊትና ባለ ራእዩ ሳሙኤል ነበሩ።
23የማደሪያውን ድንኳን፣ ማለትም የእግዚአብሔርን ቤት የሚጠብቁትም እነርሱና ዘሮቻቸው ነበሩ። 24በር ጠባቂዎቹም በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜንና፣ በደቡብ በሚገኙት በአራቱም ማእዘኖች ላይ ነበሩ። 25ወንድሞቻቸውም በየመንደሮቻቸው ሆነው በየጊዜው እየወጡ የጥበቃውን ሥራ ሰባት ሰባት ቀን ያግዟቸው ነበር። 26ሌዋውያን የነበሩት አራቱ የበር ጠባቂ አለቆች ግን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሚገኙትን ክፍሎችና ግምጃ ቤቶች በኀላፊነት ይጠብቁ ነበር። 27የጥበቃውን ሥራ የሚያከናውኑት እነርሱ በመሆናቸው የሚያድሩትም በዚያው በእግዚአብሔር ቤት አካባቢ ነበረ፤ ጧት ጧትም ደጆቹን የሚከፍቱት እነርሱ ነበሩ።

28ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በኀላፊነት ይጠብቁ ነበር፤ ዕቃዎቹም በሚገቡበትና በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ ይቈጥሩ ነበር። 29ሌሎቹ ሌዋውያን ደግሞ ዕቃዎቹንና የቤተ መቅደሱን ንዋያተ ቅድሳት፣ ዱቄቱን፣ የወይን ጠጁን፣ የወይራ ዘይቱን፣ ዕጣኑን፣ የሽቱውን ቅመማ ቅመም እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር። 30ከካህናቱም አንዳንዶቹ የሽቱውን ቅመማ ቅመም ይለውሱና ያዘጋጁ ነበር። 31የቆሬያዊው የሰሎም በኵር ልጅ ሌዋዊው ማቲትያ የቍርባኑን እንጀራ የመጋገር ኀላፊነት ተሰጥቶት ነበር። 32በየሰንበቱ ለሚዘጋጀው ገጸ ኅብስትም ኀላፊነቱ የተሰጠው ከቀዓታውያን ወንድሞቻቸው መካከል ለአንዳንዶቹ ነበር።

33የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች የነበሩት መዘምራኑ ደግሞ በቤተ መቅደሱ ክፍሎች ውስጥ እንዲኖሩና ከሌላው ሥራ ሁሉ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጎ ነበር፤ ምክንያቱም ቀንና ሌሊት የሚሠሩት ሥራ ነበራቸው።

34እነዚህ ሁሉ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሲሆኑ፣ በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት ተመዘገቡ፤ የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።

የሳኦል ትውልድ ሐረግ

9፥34-44 ተጓ ምብ – 1ዜና 8፥28-38 35የገባዖን አባት
አባት ማለት፣ የማኅበረ ሰብ መሪ ወይም፣ የጦር መሪ ማለት ነው።
ይዒኤል የሚኖረው በገባዖን ነበረ፤
የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል።
36የበኵር ልጁ ዓብዶን ሲሆን፣ የእርሱም ተከታዮች ዱር፣ ቂስ፣ በኣል፣ ኔር፣ ናዳብ፣ 37ጌዶር፣ አሒዮ፣ ዛኩር፣ ሚቅሎት ነበሩ። 38ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፤ እነርሱም ከዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።
39ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦል ዮናታንን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን
ኢሽጠቦሼት በመባልም ይታወቃል።
ወለደ።
40የዮናታን ወንድ ልጅ፤
መሪበኣል
ሜፊቦስቴ በመባልም ይታወቃል።
ነው፤ መሪበኣል ሚካን ወለደ።
41የሚካ ወንዶች ልጆች፤
ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ።
42አካዝ የዕራን ወለደ፤ የዕራም ናሌሜትን፣ ዓዝሞትን፣ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ። 43ሞጻም ቢንዓን ወለደ፤ ልጁ ረፋያ ነበረ፤ ልጁ ኤልዓሣ፣ ልጁ ኤሴል።
44ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም፦
ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሸዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን፤ እነዚህ የኤሴል ወንዶች ልጆች ናቸው።
Copyright information for AmhNASV